Detecting...
Please whitelist dirzon to continue.
በመሆኑም ታጥቆ የሚገኘው ኃይል ለሥርዓት አልበኝነት መበራከት ጉልህ ሚና ይጫወታል።
በዘላቂ ድል ወደ ብልጽግና የድኅረ ጦርነት መዛነፎችና እርምቶቹ ታህሣሥ ጋዐገ ዓም ሃዋሳ ማዉጫ ሀገራዊ ይድኅጎረ ጦርነት ፈተናዎችና አቅጣጫዎች የአዲስ አበባ ሁኔታ የአማራ ክልል ሁኔታ የአፋር ክልል ሁኔታ የኦሮሚያ ክልል ሁኔታ የሶማሌ ክልል ሁኔታ የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ሁኔታ የጋምቤላ ክልል ሁኔታ ሲዳማ ክ ልል ሁሁ ኔታ ራራ ይ የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ሁኔታ የሐረሪ ክልል ሁኔታ የድሬዳዋ አስተዳደር ሁኔታ የደቡብ ብብህዝቦች ክልል ሁኔታ ሬ ሆይ ሰሬ ሆይ ጎሩን ጳያህና ገደሐጋ ሳታይ አም ካው ገደል ወደቅክብን ወይ ሀገራዊ ብሂል መግቢያ የፖለቲካ ቅራኔዎች ወደ ግጭት አድገው ለብዙኃን እልቂትና ለንብረት ውድመት ምክንያት በመሆን በጦርነት ድምዳሜ ሊያገኙ ይችላሉ። ሆኖም ጦርነቱን በድል ያጠናቀቀው ኃይል የድኅረ ጦርነት ሁኔታውን በአግባቡ መምራት ካልቻለ የጦርነቱ ሂደት የሚፈጥረው የፖለቲካና ወታደራዊ ማኅበራዊና ሥነ ልቡናዊ መናጋት የሚወልዳቸው ችግሮች ድሉን ወደ ኋላ የሚቀለብሱና አሸናፊው ወገን ወደ አዲስ ብጥብጥ እንዲገባ የሚያደርጉ የድኅረ ጦርነት ቀውሶች ሊከሰቱ ይችላሉ። የድኅረ ጦርነት ሁኔታውን በትኩረትና በዲሲፕሊን መምራት ካልቻልን ጦርነት ውስጥ ያስገቡን ጠላቶቻችን በጦር ሜዳ ያጡትን ድል በድኅረ ጦርነት ቀውስን ለማግኘት እንዲሞክሩ ያደርጋቸዋል። ሀገራዊ የድኅረ ጦርነት ፈተናዎችና አቅጣጫዎች የአማራ ክልል ሁኔታ ሀ የፖለቲካ ሁኔታ በፖለቲካው መስክ ሊፈጠሩ የሚችሉ ሁኔታዎችን ጠቅለል አድርገን ስናያቸው በሦስት ፈርጆች ሊሠፍሩ ይችላሉ የድል ሽሚያ ፖለቲካ የይገባኛል ፖለቲካ እና የተከዳን ፖለቲካ ናቸው። ይህ የድል ሽሚያ ፉክክር በዋናነት በክልሉ የጸጥታ ኃይሎችና በፌዴራል ኃይሎች መካከል እንዲሁም በክልሉ ልዩ ልዩ ኃይሎች መካከል እንዲሁም በተለያዩ የክልሉ አካባቢዎች መካከል የሚፈጠር ሊሆን ይችላል። የአፋር ክልል ሁኔታ የኢትዮጵያን ጉሮሮ አንቃለሁ በሚል ቀቢፀ ተስፋ የጁንታው የሽብር ወረራ ካረፈባቸው ክልሎች የአፋር ክልል አንዱ ነው። ይኸውም የአንዳንድ አማጽያን ረብሻ ከሶማሊያ ጋር የሚኖረው ድንበር ሁኔታና ከአፋር ክልል ጋር የሚኖር ግጭት ሊሆን ይችላል የቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ሁኔታ ክልሉ እንደ ሌሎች ክልሎች በህልውና ዘመቻው ከፍተኛ አበርክቶ የነበረው ክልል ነው። የሰሜኑ ጦርነት ከተጠናቀቀ በኋላ በድኅረ ጦርነት ወቅት ሊከሰቱ ከሚችሉ ሁኔታዎች መካከል ክልሉ የሕወሐት ችግር መፍጠሪያ አካባቢ ሊሆን ይችላል ይሆናል የውጭ ኃይላት ኢትዮጵያን ለማጥቃት ዋነኛ አማራጫቸው እየተደካመ መሆኑን ሲረዱ ኢትዮጵያን ለማጥቃት በቤኒሻንጉል ክልል በኩል የተለያዩ አማራጮችን መጠቀማቸው አይቀርም። የጋምቤላ ክልል ሁኔታ የጋምቤላ ክልል በህልውና ዘመቻው ወቅት ቀጥተኛ የጦርነቱ ተጋፋጭ ባይሆንም ለዘመቻው መሳካት ግን ከፍተኛ ሚና ተጫውቷል። በድኅረ ጦርነት የጋምቤላ ክልል ሁኔታ የሚከተሉትን ሊመስል ይችል ይሆናል በጋምቤላ ክልል ያለው ዋነኛ ስጋት የስደተኞች ጉዳይ ነው። ሲዳማ ክልል ሁኔታ የሲዳማ ክልል በነበረው የሕግ ማስከበር እንቅስቃሴ ጉልህ ሚና የተጫወተ ነው። የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ሁኔታ ክልሉ አዲስ ቢሆንም በተቋቋመ በአጭር ጊዜ ውስጥ በህልውና ዘመቻው በሰው ኃይል በሎጀስቲክ ድጋፍና በመሳሰሉት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያደረገ ያለ ክልል ነው። የሐረሪ ክልል ሁኔታ የሐረሪ ክልል በሕልውና ዘመቻው ከመከላከያ ጎን በመሆን በሰው ኃይል በሎጀስቲክስ አቅርቦት በሞራል ፍጋፍና በመሳሰሉት ቀጣይነት ያለው አስተዋጽኦ ሲያበረክት ቆይቷል። የደቡብ ብብህዝቦች ክልል ሁኔታ የደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል ለህልውና ዘመቻው መሳካት በሰው ኃይል በሀብት ማሰባሰብና መደገፍ በሎጅስቲክ አቅርቦት የሕዝቡን የሞራል ድጋፍ በማስተባበር የአከባቢውን ሰላምና ደኅንነት በመጠበቅና በመሳሰሉት ከፍተኛ አስተዋጽኦ አበርክቷል በጦርነቱ የተጎዱ ህዝቦችን በመደገፍ ረገድም በተጨባጭ አጋርነቱን ያረጋገጠ ክልል ነዉ።